የዘወትር ጸሎት ውዳሴ ማርያም
--------------------------
በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕምርተ መስቀል ፊቴንና መላ
ሰውነቴን ሶስት ጊዜ አማትባለሁ።
፩ እግዚአብሔርን ስለማምን አንድ አምላክ በሆኑ በአብ በወልድ
በመንፈስ ቅዱስ ስም ልዩ ክብር ጽሩይ በሆኑ በሶስትነት ወይም
በስላሴ እያመንኩምና እየተማፀንኩ ጠላቴን ሰይጣንን እክዳለሁ
በዚች በእናቴ በቤተ ክርስቲያን ፊት ቁሜ እክድሃለሁ ለዚህም
ምስክሬ ማርያም ናት በዚህም ዓለም በወዲያኛውም አለም
እሷን አምባ መጠጊያ አድርጌ እክድሃለሁ።
፪ አቤቱ እናመሰግንሃለን አቤቱ እናከብርሃለን አቤቱ እንገዛልሃለን
አቤቱ ቅዱስ ስምህን እናመሰግናለን ጉልበት ሁሉ የሚሰግድልህ
አቤቱ እንሰግድልሃለን አንደበት ሁሉ ላንተ ይገዛል የአምላኮች
አምላክ የጌቶ ጌታ የንጉሶች ንጉስ አንተ ነህ። የስጋም የነፍስም
ፈጣሪ አንተ ነህ። እናንተስ በምትፀልዩበት ጊዜ እንዲህ ላችሁ
ፀልዩ ብሎ ቅዱስ ልጅህ እንዳስተማረን እንጠራሃለን።
፫. አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግስትህ
ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን፣
የእለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን እኛም
የበደሉንን ይቅር እንደምንል። ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉ
አድነን እንጂ መንግስት ያንተ ናትና ኃይል ምስጋና ለዘላለሙ
አሜን።
፬. እመቤቴ ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርሄል ሰላምታ
ሰላም እልሻለሁ በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በስጋሽም ድንግል
ነሽ።የአሸናፊ እግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባል።
ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽና የማህፀንሽም ፍሬ
የተባረከ ነው። ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር
ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን
ከእየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኝልን ኃጢአታችንን
ያስተሠርይልን ዘንድ አሜን።
የሃይማኖት መሠረት
---------------
፭ . ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ
እናምናለን።ሰማይና ምድርን የፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውን
አለም ሳይፈጠር ከርሱ ጋር በነበረ አንድ የአብ ልጅ በሚሆን
በአንድ ጌታ በእየሱስ ክርስቶስ እናምናለን ። ከብርሃን የተገኘ
ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ የተወለደ እንጂ
ያልተፈጠረ በባሕርዩ ከአብ ጋር የሚካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ
በሰማይም ካለው በምድርም ካለው ያለእርሱ ምንም የሆነ
የለም ስለኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ
ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍፁም ሰውን ሆነ
ደግሞም ስለኛ ተሰቀለ። በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ
መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረ በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ
ተነሳ በቅዱሳት መፀሐፍት እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደ
ሠማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና
በሙታን ለመፍረድ በምስጋና ይመጣል። ለመንግስቱም ፍፃሜ
የለውም። በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን
የሚሰጥ በአብ የሰረጸ ከአብ ከወልድ ጋር በአንድነት
እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን እርሱም በነቢያት አድሮ
የተናገረ ነው ከሁሉም.በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰሯት
በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን። ኃጢያት በሚሰረይባት
በአንዲት ጥምቀት እናምናለን የሙታንን መነሳት ተስፋ
እናደርጋለን የሚመጣውን ሕይወት ለዘላለሙ አሜን፣
፮. አሸናፊ እግዚአብሔር ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ
ትመሠገናለህ። ምስጋናህም በሰማይ በምድር የመላ ነው።
ክርስቶስ ሆይ ላንተ እንሰግድልሃለን ሰማያዊ ከሚሆን ከቸር
አባትህ ጋር አዳኝ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አዳኝ
እንሰግድልሃለን ወደዚህ አለም መጥተህ አድነኸናልና።
፯. ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ
፫ጊዜ በል አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ በአካል ሦስት
ሲሆኑ በመለኮት አንድ ለሚሆኑ አምላክ እሰግዳለሁ። አምላክን
ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያምም እሰግዳለሁ።
ዓለምን ሁሉ ለማዳን ሲል እየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት
መስቀል እሰግዳለሁ። መስቀል ኃይላችን ነው። ኃይላችን
መስቀል ነው የሚያፀናን መስቀል ነው፡ መስቀል ቤዛችን ነው፡
መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን
እናምነዋለን ያመነውም እኛም በመስቀሉ እንድናለን ድነናልም።
፰. ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድም ምስጋና ይገባል።
ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል ፫ጊዜ በል።
አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋና
ይገባል።ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል።
ክርስቶስ በቸርነቱ ያስበን ዘንድ ዳግመኛም በመጣ ጊዜ
እንድዳያሳፍረን ስሙን ለማመስገን ያበቃን ዘንድ እመቤታችን
ፀሎታችንን አሳርጊልን። ኃጢያታችንንም አስተሥርዪልን
በጌትልችን መንበር ፊት ፀሎታችንን አሳርጊልን ይህንን ኅብስት
ላበላን ይህንንም ጽዋ ላጠጣን ምግባችንና ልብሳችንንም
ላዘጋጀልን ኃጢያታችንንም ሁሉ ለታገሰልን ክቡር ደሙን ቅዱስ
ስጋውን ለሰጠን እስከዚህችም ሰዓት ላደረሰን ለእሱ ለልዑል
እግዚአብሔር ፍፁም ምስጋና ይገባል ለወለደችው ለድንግልም
ምስጋና ይገባል። ለክቡር መስቀሉም ምስጋና ይገባል።
እግዚአብሔር ስሙ ፈፅሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱ
በየሰዓቱ ምስጋና ይገባል።
፱. እናታችን ማርያም ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን
እንሰግድልሻለን እንማልድሻለን ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ
ተማጽነንብሻል ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ
እያቄም ብለሽ ድንግል ማኅበራችንን ዛሬ ባርኪልን።
፲. አምላክን በድንግልና የወለደች የእመቤታችን የማርያም
ፀሎት ሉቃ ፩፡፵፮-፶፬
-------------------------------------
ማርያምም አለች ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች
መንፈሴም በመድሐኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል።
የባሪያይቱን መዋረድ አይቷልና እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ
ያመሰግኑኛል። እርሱ ብርቱ የሚሆን ታላቅ ስራን ለእኔ
አድርጉዋልና። ስሙም ቅዱስ ነው። ለሚፈሩትም ምሕረቱ ለልጅ
ልጅ ነው። ኃይልን በክንዱ አደረገ። በልባቸው አሳብ የሚኮሩ
ትዕቢተኞችን በታተናቸው ብርቱዎችንም ከዙፋናቸው አዋረዳቸው
የተዋረዱትንም ከፍ ከፍ አደረጋቸው። የተራቡትንም በቸርነቱ
አጠገባቸው ባለጠጎችንም ባዶ እጃቸውን ሰደዳቸው ምሕረቱን
እንዲያስብ እስራኤል ባሪያውን ተቀበለ። ለአባቶቻችን
--------------------------
በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕምርተ መስቀል ፊቴንና መላ
ሰውነቴን ሶስት ጊዜ አማትባለሁ።
፩ እግዚአብሔርን ስለማምን አንድ አምላክ በሆኑ በአብ በወልድ
በመንፈስ ቅዱስ ስም ልዩ ክብር ጽሩይ በሆኑ በሶስትነት ወይም
በስላሴ እያመንኩምና እየተማፀንኩ ጠላቴን ሰይጣንን እክዳለሁ
በዚች በእናቴ በቤተ ክርስቲያን ፊት ቁሜ እክድሃለሁ ለዚህም
ምስክሬ ማርያም ናት በዚህም ዓለም በወዲያኛውም አለም
እሷን አምባ መጠጊያ አድርጌ እክድሃለሁ።
፪ አቤቱ እናመሰግንሃለን አቤቱ እናከብርሃለን አቤቱ እንገዛልሃለን
አቤቱ ቅዱስ ስምህን እናመሰግናለን ጉልበት ሁሉ የሚሰግድልህ
አቤቱ እንሰግድልሃለን አንደበት ሁሉ ላንተ ይገዛል የአምላኮች
አምላክ የጌቶ ጌታ የንጉሶች ንጉስ አንተ ነህ። የስጋም የነፍስም
ፈጣሪ አንተ ነህ። እናንተስ በምትፀልዩበት ጊዜ እንዲህ ላችሁ
ፀልዩ ብሎ ቅዱስ ልጅህ እንዳስተማረን እንጠራሃለን።
፫. አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግስትህ
ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን፣
የእለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን እኛም
የበደሉንን ይቅር እንደምንል። ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉ
አድነን እንጂ መንግስት ያንተ ናትና ኃይል ምስጋና ለዘላለሙ
አሜን።
፬. እመቤቴ ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርሄል ሰላምታ
ሰላም እልሻለሁ በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በስጋሽም ድንግል
ነሽ።የአሸናፊ እግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባል።
ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽና የማህፀንሽም ፍሬ
የተባረከ ነው። ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር
ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን
ከእየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኝልን ኃጢአታችንን
ያስተሠርይልን ዘንድ አሜን።
የሃይማኖት መሠረት
---------------
፭ . ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ
እናምናለን።ሰማይና ምድርን የፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውን
አለም ሳይፈጠር ከርሱ ጋር በነበረ አንድ የአብ ልጅ በሚሆን
በአንድ ጌታ በእየሱስ ክርስቶስ እናምናለን ። ከብርሃን የተገኘ
ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ የተወለደ እንጂ
ያልተፈጠረ በባሕርዩ ከአብ ጋር የሚካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ
በሰማይም ካለው በምድርም ካለው ያለእርሱ ምንም የሆነ
የለም ስለኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ
ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍፁም ሰውን ሆነ
ደግሞም ስለኛ ተሰቀለ። በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ
መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረ በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ
ተነሳ በቅዱሳት መፀሐፍት እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደ
ሠማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና
በሙታን ለመፍረድ በምስጋና ይመጣል። ለመንግስቱም ፍፃሜ
የለውም። በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን
የሚሰጥ በአብ የሰረጸ ከአብ ከወልድ ጋር በአንድነት
እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን እርሱም በነቢያት አድሮ
የተናገረ ነው ከሁሉም.በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰሯት
በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን። ኃጢያት በሚሰረይባት
በአንዲት ጥምቀት እናምናለን የሙታንን መነሳት ተስፋ
እናደርጋለን የሚመጣውን ሕይወት ለዘላለሙ አሜን፣
፮. አሸናፊ እግዚአብሔር ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ
ትመሠገናለህ። ምስጋናህም በሰማይ በምድር የመላ ነው።
ክርስቶስ ሆይ ላንተ እንሰግድልሃለን ሰማያዊ ከሚሆን ከቸር
አባትህ ጋር አዳኝ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አዳኝ
እንሰግድልሃለን ወደዚህ አለም መጥተህ አድነኸናልና።
፯. ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ
፫ጊዜ በል አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ በአካል ሦስት
ሲሆኑ በመለኮት አንድ ለሚሆኑ አምላክ እሰግዳለሁ። አምላክን
ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያምም እሰግዳለሁ።
ዓለምን ሁሉ ለማዳን ሲል እየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት
መስቀል እሰግዳለሁ። መስቀል ኃይላችን ነው። ኃይላችን
መስቀል ነው የሚያፀናን መስቀል ነው፡ መስቀል ቤዛችን ነው፡
መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን
እናምነዋለን ያመነውም እኛም በመስቀሉ እንድናለን ድነናልም።
፰. ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድም ምስጋና ይገባል።
ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል ፫ጊዜ በል።
አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋና
ይገባል።ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል።
ክርስቶስ በቸርነቱ ያስበን ዘንድ ዳግመኛም በመጣ ጊዜ
እንድዳያሳፍረን ስሙን ለማመስገን ያበቃን ዘንድ እመቤታችን
ፀሎታችንን አሳርጊልን። ኃጢያታችንንም አስተሥርዪልን
በጌትልችን መንበር ፊት ፀሎታችንን አሳርጊልን ይህንን ኅብስት
ላበላን ይህንንም ጽዋ ላጠጣን ምግባችንና ልብሳችንንም
ላዘጋጀልን ኃጢያታችንንም ሁሉ ለታገሰልን ክቡር ደሙን ቅዱስ
ስጋውን ለሰጠን እስከዚህችም ሰዓት ላደረሰን ለእሱ ለልዑል
እግዚአብሔር ፍፁም ምስጋና ይገባል ለወለደችው ለድንግልም
ምስጋና ይገባል። ለክቡር መስቀሉም ምስጋና ይገባል።
እግዚአብሔር ስሙ ፈፅሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱ
በየሰዓቱ ምስጋና ይገባል።
፱. እናታችን ማርያም ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን
እንሰግድልሻለን እንማልድሻለን ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ
ተማጽነንብሻል ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ
እያቄም ብለሽ ድንግል ማኅበራችንን ዛሬ ባርኪልን።
፲. አምላክን በድንግልና የወለደች የእመቤታችን የማርያም
ፀሎት ሉቃ ፩፡፵፮-፶፬
-------------------------------------
ማርያምም አለች ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች
መንፈሴም በመድሐኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል።
የባሪያይቱን መዋረድ አይቷልና እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ
ያመሰግኑኛል። እርሱ ብርቱ የሚሆን ታላቅ ስራን ለእኔ
አድርጉዋልና። ስሙም ቅዱስ ነው። ለሚፈሩትም ምሕረቱ ለልጅ
ልጅ ነው። ኃይልን በክንዱ አደረገ። በልባቸው አሳብ የሚኮሩ
ትዕቢተኞችን በታተናቸው ብርቱዎችንም ከዙፋናቸው አዋረዳቸው
የተዋረዱትንም ከፍ ከፍ አደረጋቸው። የተራቡትንም በቸርነቱ
አጠገባቸው ባለጠጎችንም ባዶ እጃቸውን ሰደዳቸው ምሕረቱን
እንዲያስብ እስራኤል ባሪያውን ተቀበለ። ለአባቶቻችን
ለአብርሃምና ለዘሩም እስከ ዘለዓለም ድረስ እንደተናገረው።
ቅዳሜ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል
ማርያም ምስጋና።
1. ንጽሕት ነሽ ብርህትም ነሽ። ጌታን በመካከል እጅ የያዝሽው
ሆይ በሁሉ የተቀደሽ ነሽ። ፍጥረት ሁሉ ቅድስት ሆይ ለምኝልም
ብለው እየጮኹ ካንቺ ጋር ደስ ይላቸዋል።
2. ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። ባለሟልነትን አግኝተሻልና
ደስ ይበልሽ። እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ።
ግርማ ያለሽ ድንግል ሆይ ገናንነትሽን እናመሰግናለን
እናደንቃለን። እንደ መልአኩ ገብርኤልም ምስጋና
እናቀርብልሻለን የባሕርያችን መዳን በማህጸንሽ ፍሬ ተገኝቷልና።
ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
3. እንደ ሠርግ ቤት ጉድፍ የሌለብሽ ነሽ መንፈስ ቅዱስ
አድሮብሻልና የልዑል ኃይልም ጸልሎሻልና። ማርያም ሆይ
ለዘለዓለም የሚኖር መጥቶ ከኃጢያት ያዳነን የአብ ልጅ ቃልን
በውነት ወለድሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
4. ከዳዊት ሥር የተገኘሽ ባሕርይ (ዘር) አንቺ ነሽ።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ ወልደሽልናልና። ከአብ
የተወለደ ከዓለም በፊት የነበረ አንዱ ቃል ራሱን (ባሕርዩን)
ሰወረ። ካንቺም የተገዥን (ሰውን) አርአያ ነሣ።ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
5. አምላክን ያለርኩሰት የወለድሽው ሆይ የምድር ሁለተኛ ፀሐይ
ካንቺ ወጥቶልናልና። እንደነቢያት ትንቢትም ያለዘርና
ያለመለወጥ ወለድሽው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።
6. ከተለዩ የተለየች የተባልሽ የኪዳን ጽላት ያለብሽ የተሰወረ
መና ያለበት የወርቅ መሶብ ያለብሽ ደብተራ ድንኳን አንቺ ነሽ።
ይኸውም መና የተባለው መጥቶ በድንግል ማርያም ያደረው
የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የአብ ቃል በርስዋ ሰው ሆነ መጥቶ
ያዳነን የባሕርይ ንጉሥን በዓለም ውስጥ የወደችው የሚናገር
በግ የክርስቶስ እናቱ ገነት ደስ ይላታል ለዘላለም የሚኖር የአብ
ልጅ እርሱ መጥቶ ከኃጢአት አድኖናልና።ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
7. የንጉስ ክርስቶስ እናቱ ተባልሽ እርሱን ከወለድሽ በኋላም
በድንግልና ኖርሽ። ድንቅ በሆነ ምሥጢር (ተዋህዶ) አማኑኤልን
ወለድሽው ስለዚህም ባለመለወጥ አጸናሽ።ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
8. እግዚአብሔር በላይዋ ተቀምጦባት ያዕቆብ ያያት መሰላል
አንቺ ነሽ። በሁሉ በኩል የማይመረመር እርሱን ተፈትሖ በሌለበት
ማህፀንሽ ተሸክመሽዋልና። እኛን ስለማዳን ካንቺ ሰው በሆነ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ አማላጅ ሆንሽን።ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
9. የተባረክሽ ንጽህት የሆንሽ አዳራሽ ሆይ እንሆ ጌታ የፈጠረውን
ዓለም ሁሉ በይቅርታው ብዛት ያድን ዘንድ ካንቺ ወጣ (ተወለደ)
ፈጽመን እናመስግነው። ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና።ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።
10. ያለርኩሰት ድንግል የሆንሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ
ይበልሽ። የዓለም ሁሉ ምክበርያ ጽዋ ነሽ። የማትጠፊ ፋና ነሽ
የማትፈርሽ መቅደስ ነሽ። የቅዱሳን መደገፊያቸው
(መጠጊያቸው) የማትለወጪ የሃይማኖት በትር ነሽ። ቸር
አዳኛችን ወደ ሆነ ልጅሽ ለምኝልን ፈጽሞ ይቅር ይለን ይምረን
ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ።ቅድስት ሆይ
ለምኝልን።